የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ከሳዉዝ ኮርያ የመጡ ልኡካን ቡድኖች ጋር ዉይይት አካሄዱ
ITDB፦ ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ከሳዉዝ ኮርያ የመጡ ልኡካን ቡድኖች ጋር ዉይይት አካሄዱ። የዉይይት መርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ government decision support system (GDSS) ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመሆን ለከተማ አስተዳደሩ የማልማት ሂደት ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።
በዉይይቱም የቢሮ ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላትና ከሳዉዝ ኮርያ የመጡ ልኡካን ቡድኖች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ መዲናችን በርካታ ሀብት እንዳላትና አብሮነቱ ከተማዋን ስማርት ከማድረግ አንፃር የጎላ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀዉ በዚህ ዉይይት አብሮነትን የምናስቀጥልበትና በጋራ ለመስራት የተዘረጋ ትልቅ ድልድይ መሆኑን አመላክተዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የስማርት ሲቲ ፅንሰ ሀሳብ እና ስድስት አምዶች እንዲሁም ዲጅታል ሰርቪስን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከዚህም ባሻገር በተቋሙ ለምተዉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ሲስተሞች አመላክተዋል።
በቀረበዉ ገለፃ ላይ መሰረት ያደረገ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የቀረብ ሲሆን የስማርት ሲቲ ዘርፍ
ም/ቢሮ ሀላፊ ምላሽ በመስጠትና የአንድነት ስሜትን በመፍጠር መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714"
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments