የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የቢሮ የሰዉ ሀብት ዳይሬክተር ወ/ሪት ፀሀይ በዳዳ የሙያ ስነ-ምግባር በሚል ርዕስ ስር የሙያ ስነ-ምግባር ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ የሙያ ስነ-ምግባር መሰረታዊ ነጥቦች፣ ቁልፍ የሚባሉ የሙያ ስነ-ምግባሮች፣ የስራ ስነ-ምግባር፣ በስራ ቦታ ላይ የሚታዩ የስራ ስነ-ምግባር ጉድለቶች፣ ለስነምግር ጉድለቶች እንደ ምክንያት የሚቀርብ ሰበቦች፣ የስራ ሰነ-ምግበርን ለማጠናከርና ለማጎልበት የሚረዱ መንገዶች ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእዉቀት ሽግግሩ መልካም እንደነበርና ከሙያ ስነምግባርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የነበራቸዉ ተሞክሮ ያካፈሉ ሲሆን በሳምንቱ የሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር በመማመላከት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments