"የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች"...

image description
- In Training    0

"የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የህዝብ ዉይይት መድረክ ተካሄደ

ITDB፦ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም

የዉይይት መርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ህዝብና መንግስት ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚነሱበትና በጋራ መፍትሄ የሚሰጥበት፣ ወቅታዊ ከተማዊ፣ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የማድረስ ስራ የሚከናወንበት ሲሆን ከዚህም ባሻገር በህብረተሰብ ዘንድ ብዥታ የፈጠሩ ሀሳቦችን የማጥራት ስራ ማከናወን ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

በመርሃ-ግብሩ የወረዳ ካቢኔ አባላት የክ/ከተማ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች የተገኙ ሲሆን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ባለፉት ሰባት ዓመታት በርካታ የለዉጥ ተግባራት መከናቸዉንና ከመንግስት ጎን በመቆምና በመደገፍ የህዝብ ሚና የጎላ እንደነበር ገልፀዉ ለሚኩራ ክ/ከተማ የመዲናችንን የከፍታ ማማ ማሳያ ከሆኑ ክ/ከተማዎች አንዱ መሆኑንና የዲሞክራሲ ምህዳርን ለማስፍት እንዲሁም ለነዋሪዎችዋ ምቹ የሆነ ከተማን ለመገንባት በጋራ አብሮ መስራት እንደሚገባ በማመላከት በዛሬዉ መርሃ ግብር ላይ በነፃነት ሀሳብና አስተያየት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዉ መርሃ ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።

በተያያዘም የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ህይወት ዳኜ የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች፣ በክ/ከተማዉና ወረዳዉ በለዉጥ ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ያቀረብ ሲሆን በቀረበዉ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉና የክ/ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማካኝነት ተካሂዷል።በዉይይቱም የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ሀሳቦቹን እንደግብአት በመዉሰድ የዉይይት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments