"የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የህዝብ ዉይይት መድረክ ተካሄደ
ITDB፦ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም
የዉይይት መርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ህዝብና መንግስት ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚነሱበትና በጋራ መፍትሄ የሚሰጥበት፣ ወቅታዊ ከተማዊ፤ ሀገራዊ፤ ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የማድረስ ስራ የሚከናወንበት ሲሆን ከዚህም ባሻገር በህብረተሰብ ዘንድ ብዥታ የፈጠሩ ሀሳቦችን የማጥራት ስራ ማከናወን ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።
በመርሃግብሩ የወረዳ ካቢኔ አባላት የክ/ከተማ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች የተገኙ ሲሆን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ከተማችን ላለፉት ሰባት አመታት የለዉጥ ሂደት ላይ መሆኗን ገልፀዉ የከተማ አስተዳደሩ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ቆራጥ የሆነ ስራን በመስራት ላይ መሆኑንና 1538 ፕጀክቶችን አጠናቆ የማስመረቅ ስራ መሰራቱን ጠቁመዉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትና ፈጣን ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አየተሰጠ መሆኑን በማመላከት መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።
በተያያዘም የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለሜሳ ነገረ የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች በሚል ርዕስ ሰነድ ያቀረብ ሲሆን በቀረበዉ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና የክ/ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማካኝነት ተካሂዷል።በዉይይቱም የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ሀሳቦቹን እንደግብአት በመዉሰድ የዉይይት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments