በአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ከአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ
ITDB፦ ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም
የልምድ ልዉዉጡ ዋና ዓላማ የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሊያደርግ ያሰበዉ የሪፎርም ስራ ዙርያ የእዉቀት ሽግግርና የልምድ ልዉዉጥ ማድረግ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን አማካኝነት ዲጅታል ጋለሪዉን፣ የስማርት ሲቲ ሮድማፕና ስድስት ምሶሶዎች እንዲሁም ዲጅታል ሰርቪስ፣ የቢሮዉን መዋቅር፣ በዉስጥ አቅምና አማካሪዎች የለሙ ሲስተሞች የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸዉ ደስተኛ እንደነበሩ እንዲሁም ቢሮዉ ሳቢና ለስራ ምቹ የሆነ ከባቢ እንዳለዉ በመግለፅ እገዛ የሚሹባቸዉን ርዕሰ ጉዳዮች በዝርዝር አብራርተዋል። በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ቢሮዉ በየትኛዉ እንቅስቃሴ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸዉ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments