የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ያለማዉ የአምራች ኢንዱስትሪ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት (IIMS) በይፋ ተመረቀ

ITDB ህዳር/2018

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ያለማዉ የአምራች ኢንዱስትሪ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት (Integrated Industry Management Information System) አስመርቋል።

በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂዉን ላለማዉ አካል ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የለማው ቴክኖሎጂ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ምዝገባ እስከ ምርት ምዝገባ ያለውን መረጃ የያዘ መሆኑንና አምራች ኢንዱስትሪዎች በኦንላይ መረጃ እንዲያገኙ ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ገልጸው ቴክኖሎጂው 12 ዋና እና 31 ንኡስ አገልግሎት መያዙን ጠቁመዋል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በበኩላቸው የለማው ሲስተም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ቀልጣፋ ፈጣንና ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስች አመላክተዋል።

በመጨረሻም የለማውን ሲስተም የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን ባለድርሻ አካላት እና በየደረጃው ያሉት አመራሮች የለማውን ሲስቲም በመጠቀም ለአምራች ኢንዱስትሪው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments