የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ
ITDB፦ህዳር 22/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዲዛይን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ሚካኤል በራስ መተማመን እጦት፣ የሚያስከት ጉዳት፣ ህክምናዉ ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በራስ መተማመንና አመራርነት ከራስ እንደሚጀምር እንዲሁም ስራችንን በአግባቡ በመስራት ከጠባቂነት መንፈስ መላቀቅ እንደሚገባ በማመላከት በሳምንቱ የሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር በመማመላከት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments