የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ
ITDB፦ህዳር 15/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው፣ ዳይሬክተሮች እና ባለ ሙያዎች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሶፍትዌር ፕላትፎርም ልማት ዳይሬክተር አቶ ከድር ከተማ የግዜ አጠቃቀምን በተመለከተ የሰው ልጅ ኑሮ ከውልደት እስከ ሞት ደስታ ሃዘን ስኬት ውድቀት የመሳሰሉት ሁነቶች በጊዜ ውስጥ የሚፈፀሙ ስለመሆኑና ያለንን ውስን ጊዜ በአግባቡ መጠቀም እንዳለብን ጠቁመዉ አሰፈላጊና በተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጡ ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ በቂ ጊዜ መስጠት እንዳለብንና በተቃራኒው ጊዜያችንን ከሚያባክኑ ጉዳዮች የጊዜ አጠቃቀማችን መገደብ እንዳለበት አሰገንዝበዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments