"ትዉልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚ...

image description
- In Training    0

"ትዉልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ተከበረ

ITDB፦ ህዳር 15/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ትዉልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ተከበረ።

የመርሃ-ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና ጥገና ዳይሬክተር አቶ ድርሻዬ ካሰኝ ዕለቱ በተለያዩ ተቋማት እየተከበረ መሆኑንና ቀኑን ከማክበር ባሻገር የህይወት መርሃችንና የየዕለት ተግባራችን በማድረግ ከሙስና የፀዳ ተቋምና ሀገር ልንገነባ እንደሚገባ ገልፀዉ መርሃ-ግብሩን ላዘጋጀዉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተያያዘም ዕለቱን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት የቢሮ አቅም ግንባታና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ አመሀ ሲሳይ ዕለቱን ማክበር ለምን እንዳስፈለገ፣ የስነ ምግባር ምንነት፣የስነ ምግባር ምንጮች እና እንዴት እራሳችንን በስነ ምግባር መገንባት እንደሚገባን በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን በመጨረሻም የሰዉ ሀብት ዳይሬክተር ወ/ሪ ፀሀይ በዳዳ ስነ ምግባር ከራስ እንደሚጀምርና ተግባርና ሀላፊነታችንን በአግባብ መወጣት አንዱ ማሳያ መሆኑን አመላክተዉ እራሳችንን ብሎም ተቋማችንን ከዚህ ከፍ ሲል ሀገራችንን ከሙስና ለማፅዳት የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እናበርክት ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም በተሰጠዉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየት በማንሳት እና በመወያየት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments