በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በአዲስ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ

ITDB ጥር 25/2018 ዓ.ም

በስልጠናዉ የቢሮ ሰራተኛና ዳይሬክተሮች የተገኙ ሲሆን የስልጠናዉ ዓላማ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 87/2017 ላይ ሰራተኛዉ በቂ ግንዛቤ ማግኘት እንዲችና መብትና ግዴታዉን ጠንቅቆ እንዲያዉቅ ማስቻል ነዉ። ስልጠናዉ በሰዉ ሀብት ዳሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት የፐብሊክ ሰርቪስ የሰዉ ሀ/ሰ/አ/የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ስትራቴጂ፣ የአዋጅ መነሻ ሁኔታዎች አምስት መልካም እሴቶች፣ የሰራተኞች ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ,የስራ ስምሪት እና ነፃ ገለልተኛ ስርዓት፣ የመንግስት ሰራተኛ ስልጠና አሰጣጥ ስርዓት፣ የደመወዝ ስኬል, አበል, ክፍያና ጥቅማጥቅም, አገልግሎት አሰጣጥ, ቀጣይነት ያለዉ የለውጥ ዝግጅት፣ ሰራተኛን ከስራ አግዶ ስለማቆየትና የስራ ከባቢ ጤንነት ደህንነት ዓላማና ተፈፃሚነት ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱላቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments