የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በአዲስ አበባ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገመገመ
ITDB፦ ጥቅምት 7/ 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሚደግፋቸዉ ዘጠኝ ተቋማት መካከል አንዱ ነው። በመሆኑም የግምገማ ዓላማ የቢሮው የ2018 አንደኛ ሩብ ዓመት አጀማመር፣ የዝግጅት ምዕራፉ ምን እንደሚመስል፣ ከ2017 በጀት ዓመት መነሻ በማድረግ ወደ አዲሱ በጀት ዓመት የተሻገሩ ጉዳዬች ምን ላይ ናቸዉ የሚለዉን መገምገምና ክፍተቶች ካሉ ድጋፍ ማድረግ ላይ ያለመ ነው።
የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያዉ 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት በማድረግ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተዋል። ከነዚህም መካከል ከአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር ጋር በተያያዘ የኔትወርክ መቆራረጥን በዘላቂነት ለመፍታት ምን ታቅዷል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃን ከመቀባበል አንፃር ኮርፖሬት ኢሜል ለመጠቀም ግንዛቤን ከመፍጠር አንፃር ምን እየተከናወኑ ነዉ፣ የበጎ ፈቃድ ስራ ከክረምት ባለፈ በመደበኛ ጊዜ የሚከናወንበት መንገድ መመቻቸቱን፣ ሴቶችን ከማብቃትና በቂ የሰዉ ሀይልን ከመፍጠር እንዲሁም ጥቅማጥቅምን ከማስከበር አንፃር ምን እየተከናወነ ነዉ፣ የተገልጋይ እርካታንና ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ ምን እየተሰራ ነዉ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዬች በዋናነት ተነስተዋል።
በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ላይ የሚመለከታቸዉ አካላትና ም/ቢሮ ሀላፊዎችና ፅ/ቤት ሀላፊ ምላሽ የሰጡበት ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ከተማ ለመፍጠር ቢሮዉ እየሰራ መሆኑንና በራስ አቅም ሲስተሞችን የማልማት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዉ የለሙ ሲስተሞችን ከመከታተል እና ከመቆጣር አንፃር አሁን ያለዉ የቁጥጥር ስርዓት በተሻለ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑ በመግለፅ የምክር ቤቱን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዬች አስቀምጠዋል። ከተቀመጡ ጉዳዮች መካከል በዋናነት ባለሙያን ከማቆየት አንፃር የደመወዝ ጭማሪንና ግብዓትን በተመለከተ ድጋፍ እንደሚሹ አመላክተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ጋትዌች በነበራቸዉ ቆይታ ደስተኛ እንደነበሩና ቢሮዉ ለምናየዉ የቴክኖሎጂ ለዉጥ ሁሉ መሰረት መሆኑን ገልፀዉ ክፍተት የማስተዋልባቸዉ የስራ መደቦች መሟላት እንዳለባቸዉና የምክር ቤቱ ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮችን በዝርዝር ማስገባት አንደሚገባና ምክር ቤቱ የተቻለዉን ሁሉ እንደሚያደርግ አመላክተዋል። በመጨረሻም ቢሮዉ ያደራጀዉን ስማርት ጋለሪና ሶፍትዌር ዲቨሎፕመንት ላይ ስልጠና እየወሰዱ የነበሩ የተቋሙ ሰራተኞች ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments