በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሰንደቅ ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል
ITDB፦ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም
18ኛው የሰንደቅ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ' በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
በመርሃግብሩ ላይ የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ሰንደቅ ዓላማ በአንድ መሠብሠቢያችን የሆነ የሉዋላዊነታችን እና የአንድነታችን መገለጫ መሆኑን ገልፀዉ የፀጥታ አካላት ለሀገር ሰላም፣ ሉአላዊነት፣ የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ከትላንት እስከ ዛሬ የሚዋደቁት ህወታቸውን እና ደማቸውን የሚገብሩት የሀገር መገለጫ ምልክታች ሰንደቅ ዓላማን መሆኑን በመላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments