የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት አፈጻፀም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ
ITDB፦ መስከረም 28/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባዘጋጀው መድረክ በ2018 የበጀት አመት አፈፃፀም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች እና አጠቃላይ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን የተለያዩ ተቋማትና የክፍለ ከተማ ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዉ ቢሮ ባለፈው በጀት ዓመት 19 ፕሮጀክቶች መመረቃቸውንና በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ከክልሎች አንፃር 300 አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት መጀመሩን በማመላከት እራስን በቴክኖሎጂ ከማብቃት አንፃር በከተማ አስተዳደሩ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና 350 ሺህ በላይ ሰዎች መሰልጠናቸውን በመጠቆም መርሃ ግብሩን በይፍ አስደምረዋል።
የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግሩም አብተው የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም፣ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን እና የመጀሪያውን ሩብ አመት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በ2017 በጀት አመት አፈፃፀም መልካም እንደነበር አንስተው በነበረውም የአሰራር ሂደት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገልጋዮች እርካታ ከፍተኛ እንደሆነ በተደረገው ጥናት የተረጋገጠ መሆኑን ገልፀዉ ከአበይት ተግባራት አፈፃፀም ውስጥ በተቀናጀ የቴከኖሎጂ አጠቃቀም እንደ ከተማ የተገኙትን አለም አቀፍ ሽልማቶች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የተቋማት አቅም ግንባት፣ ኢትዮ-ኮደርስ፣ የዲጂታል አሰራር ላይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ፣የድህረ ገፅ ልማት፣ የደህንነት ካሜራዎች መስራትና መቆጣጠር፣ የሳይበር ደህንነት ላይ የተሰሩትን ስራዎች በስፋት የዘረዘሩ ሲሆን የነበሩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችም በሪፖርቱ ተካተዋል፡፡
በተያያዘም የ2018 በጀት አመት እቅድ የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀምን ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀረበዉ ሪፖርትና እቅድ ላይ መሰረት ያደረገ ሃሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ቀርበውበታል የቀረቡት ሀሳብ አስተያየቶችን እንደግብዓት በመዉሰድ የቢሮው አመራሮች ግብረ መልስ የሰጡ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ መልካም አፈጻጸም ላሳዩ የስራ ዘርፎች፣ ክፍለ ከተሞች እና ባለድርሻ አካላት የዕውቅና ሽልለማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments