"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ዉይይት ተካሄደ
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ዉይይት አካሄዱ።
በዉይይት መርሃ-ግብር ላይ የቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና አጠቃላይ ሰራተኛው የተገኙ ሲሆን የመወያያ ሰነዱን ያቀረብት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ፖለቲካ ማለት ሀገራዊ ዓላማንና ብሔራዊ ጥቅምን ከማስጠበቅ ጋር የተቆራኘ መሆኑንና የአባይ ወንዝ እና ቀይ ባህር የሁላችንም ብሔራዊ አጀንዳዎች እንዲሁም ጥቅሞች መሆናቸዉን ገልፀዉ በነዚህ የለዉጥ ዓመታት በዋናነት ሶስት ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣታቸውን አመላክተዋል። ያስመዘገብናቸዉን ድሎች ተከትሎ በህወሓት ዉስጥ የተፈጠሩ ስጋቶች፣ የጂኦስትራቴጂያዊ ለዉጥና የሀገር ለዉጥ፣ ዓለም ከሉዓላዊነት ወደ አዲስ የጂኦስትራቴጂያዊ የበላይነት፣ የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ መልክዓ አይኖች፣ በታደሰ ቁመና አዲሱን ዓመት መዋጀት፣ በመክሰም ስጋት ዳግም ወደ ጦርነት፣ ድልን በማላቅ የዘመናት ጥፋትን መቋጨት የሚሉ ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ሰፊ ማብራርያ ተሰጥተዋል።
በተያያዘም ሰነዱ ላይ መሰረት ያደረጉ ሀሳብ አስተያየቶች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን ሀሳቦችን እንደግብዓት በመዉሰድ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል።የዛሬው ዉይይት ዓላማ ለመንግስት ሰራተኛዉ ግንዛቤን በማስጨበጥ ወደ ህብረተሰብ ማዉረድ መሆኑን ገልፀዉ የተከተልነዉ ለዉጥ ቁጭት የወለደዉና ከኩስምንና ለመዉጣት አሰባሳቢ ትርክት መገንባት እንደሚገባ በማመላከት ትዉልዱ ላይ አተኩረን በመስራት ጥራት ያለዉ ዕድገት ማምጣት እንዳለብን ጠቁመዋል። አክለዉም የምናስከብረዉ ብሔራዊ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ፅኑ አቋም መገንባት እንደሚገባን ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments