የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ማስተላለፍ መርሃ ግብር ተ...

image description
- In Training    0

የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ማስተላለፍ መርሃ ግብር ተካሄደ

መስከረም 26/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሰኞ ማለዳ የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር የዕውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡ በመርሃ ግብሩ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆኑ መርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ በዚህ ሳምንት በተገኙት ስኬቶች በተለይ የካሉብ ጋዝ ስራ መጀመር እና የእሬቻ ክብረ በዓል በሰላም መጠናቀቁን በተመለከተ የተሰማቸዉን ደስታ በመግለፅ

መርሃ-ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።

የዕለቱን የዕዉቀት ሽግግር ያደረጉት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ከሚል መፀሀፍ "የአባይን ልጅ ለምን ውሃ ጠማው" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ መሰረት በማድረግ ዕውቀት ሽግግር አድርገዋል፡፡ በዕዉቀት ሽግግሩ የሃገራችን በስልጣኔ ወደ ኃላ መቅረት ምክንያት የሆኑትን ነገሮች፣ ትክክለኛ ጥያቄ አለመጠየቅ ፣ የባከነ እምቅ አቅም መኖር፣ የመሰረተ ልማት እጥረት፣ ስርአታዊና መዋቅራዊ ፈተናዎች እና ጦርነትና ግጭት መኖር ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የኢትዮጵያ የስልጣኔ ታሪክ አካሄድ ቀድመው ከነበሩት መንግስታት አንፃር ምን ይመስል እንደነበረ እና የነበሩ ክፍተቶች አመላክተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments