የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ መረጃ ለማደራጀት የሚያስችል ኢትዮ ኮደርስ ማኔጅመንት ሲስተም ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ITDB፦ መስከረም 22/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል። ከነዚህም ተግባራት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተጀመረው አምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ላይ ማህበረሰብን ተሳታፊ ከማድረግ አንፃር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል።
የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ የዛሬዉ
መርሃ-ግብር ዋና ዓላማ ሲስተም አጠቃቀሙን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ በስጠትና ወደ ስርዓቱ በማስገባት ከመንግስት ተቋማት ባሻገር የግል ተቋማት ስልጠናዉ ተካፋይ እንዲሆኑ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በክ/ከተማዎች እንዲከወን መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም በዛሬው ዕለት የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ አራት ኮርሶች፦ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አንድሮይድ ዲቨሎፕመንት፣ ፕሮግራሚንግና ዳታ አናላይስስ የወሰዱ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ለማደራጀት የሚያስችል ኢትዮ ኮደርስ ማኔጅመንት ሲስተም ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። በዚህ ሲስተም አተገባበር ዙርያ ለ11ዱ ክ/ከተማ ICT አስተባባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ክ/ከተማዎችን ወደ ሲስተሙ የማስባት ተግባር ተከናውኗል።
ይህንን ሲስተም በመጠቀም ምን ምን ተግባራትን ማከናወን እንደሚቻል በቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን በዚህ ሲስተም አማካኝነት በየተቋማቱ ኢትዩ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ ስንት መድረክ እንደተፈጠረ፣ ምን ያህል ሰዉ እንደተሳተፈ፣ የዕቅድና ሪፖርት ልዮነት እንዳይፈጠር፣ አፈፃፀም እንዲጨምርና የጠራ መረጃን በቁጥርና በፆታ እና ለመያዝ እንደሚጠቅም ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments