
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ እያስለማ ያለውን ሲስተም ያለበት ደረጃ ተገመገመ
በግምገማው የቢሮ አመራሮችና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የተገጙ ሲሆን የግምገማዉ ዋና ዓላማ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ አከራይ ተከራይ ዉል ምዝገባ አስተዳደር ስርዓትን ለመፍጠር የተሰራዉን ሲስተም ምን ላይ እንዳለ እና ከዚህም ባሻገር መካተት የሚገባቸዉን ርእሰ ጉዳዩች ላይ ሰፊ ዉይይት ማድረግ ነዉ፡፡
በመሆኑም በግምገማዉ ላይ አከራይ ተከራይ የውል ምዝገባ እና አስተዳደር ወቅታዊ ሁኔታ፣ የስርዓቱ ቁልፋ ባህሪያት፣ የትግበራ ስልቶች፣ የባለድርሻ አከላት ተሳትፎ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ያለዉ ጠቀሜታ በዝርዝር ተዳሷል በመሆኑም ሲስተሙ ተለዋዋጭ (dynamic) ተጨማሪ ነገሮችን ማካተት የሚቻል መሆኑ የተመላከተ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በአጭር ግዜ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments