በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን የሚሆን የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት አካሄደ
መስከረም 14/2018 ዓ.ም
የዉይይት መርሃ- ግብሩ ላይ የቢሮ ሀላፊና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የመርሃ-ግብሩ ዋና ዓላማ ለልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ዘመናዊ ፈጣንና የአሰራር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማድረግ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ ቢሮዉ የተቋማትን አሰራር ስርዓት ከማዘመን እንፃር በረካታ ተግባራት እየፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ባለስልጣን መስርያቤቱን በሙሉ አቅሙ ቴክኒካል ኮሚቴ በማዋቀር እንደሚያግዘዉ በማመላከት ሲስተም ከማልማት ባሻገር የዕዉቀት ሽግግር ስራም እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments