የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ሰራተኞች የመስቀል እና እሬቻ በዓላት አከባበር ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት አካሄደ።
ITDB፦ መስከረም 9/2018 ዓ.ም
የዉይይት መርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ በአያሌ ቅርሶች እና እሴቶች የበለፀገች ሀገር መሆንዋን ሀገራዊና ዓለም አቀፍዊ ግንዛቤ ማሳደግ፣ የመስቀል እና እሬቻ በዓላትን ባህላቸውን እና እሴታቸው ጠብቀው እንዲሰሩ በማድረግ እሴቶችን ለሀገር ግንባታ በማዋል በዓላቱ ለከተማችን እና ለሀገራችን የኢኮኖሚ ቱሪዝም ዕድገት ምንጭ ማድረግ ነዉ።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛቸዉ ፈለቀ የዘንድሮ መስቀል እና እሬቻ በአላትን ስናከብር ሁለት አበይት ጉዳዮችን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ እነዚህም ኢትዮጵያን ከዉስጥና ከዉጭ ባንዳ በመከላከል ሀገራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ቃል የምንገባበትና የህዳሴ ግድባችንን በተባበረ ክንዳችን አጠናቀን በማስመረቅ ሀገራችን በቀጠናው ያላትን ጂኦስትራቴጂካዊ ቁመናችንን ማደስ በጀመርን ማግስት መሆኑ ልዩ እንደሚያደገዉ ገልፀው በዓላቱ የኛ ብቻ ሳይሆን የዓለም ህዝብ ቅርስ መሆኑን፣ በዓላቱ እሴቶቻቸዉን ትዉፊቶቻቸዉን ጠብቆ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ ስለመፍጠር አስፈላጊነት፣ በዓላቱን ስናከብር ከከተማዋ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በዝርዝር ዳሰዋል።
በተያያዘም የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን አጉልተው የሚያሳዩ ዓመቱ ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን የምትሸጋገርበት እንደሆነ በግልጽ መልዕክት የማስተላለፍ ስራ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በወርሃ መስከረም በርካታ በዓላት እንደሚከበሩና በእነዚህ በዓላት በርካታ የሀገር ዉስጥና የዉጪ ዜጎች ወደ መዲናዋ እንደሚመጡ በማመላከት በዓላቱን በሰላማዊ መንገድ ለማክበር እንደመንግስት ሰራተኛ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባንና ከአቅም በላይ የሆኑ ነገሮችን ካስተዋልን ለሚመለከታቸዉ የፀጥታ አካላት ማሳወቅ እንደሚገባ ገልፀዉ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች በመቀበል የዉይይት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments