በአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ከሶማሌ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የልማድ ልዉዉጥ አካሄዱ።
ITDB፦ መስከረም 9/2018 ዓ.ም
የልምድ ልዉዉጡ ዋና ዓላማ በቴክኖሎጂ፣ በሪኢኖቬሽንና ዲጅታላይዜሽን ስማርት ሲቲ ዙርያ የእዉቀት ሽግግርና የልምድ ልዉዉጥ ማድረግ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ነብዩ ፍቃዱ አማካኝነት ዲጅታል ጋለሪዉን፣ የስማርት ሲቲ ሮድማፕና ስድስት ምሶሶዎች እንዲሁም ዲጅታል ሰርቪስ፣ የቢሮዉን ስትራክቸር፣ በዉስጥ አቅምና አማካሪዎች የለሙ ሲስተሞች፣ አዲስ መሶብን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸዉ ደስተኛ እንደነበሩ እንዲሁም ቢሮዉ ሳቢና ለስራ ምቹ የሆነ ከባቢ እንዳለዉ በመግለፅ እገዛ የሚሹባቸዉን ርዕሰ ጉዳዮች በዝርዝር አብራርተዋል። በመጨረሻም ምክትል ቢሮ ሀላፊዊ ቢሮዉ በየትኛዉ እንቅስቃሴ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸዉ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments