በአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ከአማራ ክልል ምክር ቤት የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የልማድ ልዉዉጥ አካሄዱ።
ITDB፦ መስከረም 8/2018 ዓ.ም
የልምድ ልዉዉጡ ዋና ዓላማ በቴክኖሎጂ፣ በሪኢኖቬሽንና ላንድ እስኬፕ ዙርያ የእዉቀት ሽግግርና የልምድ ልዉዉጥ ማድረግ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊዎች ዶ/ር ቱሉ ጥላሁንና አቶ ነብዩ ፍቃዱ አማካኝነት ዲጅታል ጋለሪዉንና ቢሮዉን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸዉ ደስተኛ እንደነበሩ እንዲሁም ቢሮዉ ሳቢና ለስራ ምቹ የሆነ ከባቢ እንዳለዉ በመግለፅ እገዛ የሚሹባቸዉን ርዕሰ ጉዳዮች በዝርዝር ከአብራርተዋል። በመጨረሻም ምክትል ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ቢሮዉ በየትኛዉ እንቅስቃሴ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments