የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተካሄደ
ITDB፦ መስከረም5/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በየሳምንቱ የሚያከናውነው እና የእውቀት ሽግግር የሚደረግበት የወርቃማው ሰኞ የአመራሮችና ሰራተኞች የተገኙበት ሲሆን የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ‘’የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው’’ በሚል ርዕስ በድምቀት በተመረቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል፡፡
ታላቁ የህዳሴ ግደብ ለቀጣይ የልማት መስኮች መሰረት የሆነ፣ለሀገራዊ ትርክት እና ለሀገረ መንግስት ግንባታ መደላድል የፈጠረ፣የቆየ ጥርጣሬ እና ፍጥጫን ወደ ጠረንጴዛ ያመጣ፣የጋራ ተጠቃሚነት ትስስር የፈጠረ እንዲሁም ለተፋሰሱ ልማት የጋራ ትብብርን ያሳየ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆማቸው እና በመሰባሰባቸው ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ማጠናቀቅ መቻሉን አመላክተዉ የተጀመረውን ለውጥ እንድናስቀጥል እና ለሌሎች ምሳሌ እና አርአያ ለመሆን መትጋት እንደሚገባ ጠቅሰው የህዳሴ ግዱቡን ለማጠናቀቅ ባለፉት 14 ዓመታት ለግድቡ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
በተያያዘም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን በግድቡ የተጀመረው ትብብርና አንድነት መቀጠል እንዳለበትና ቀጣይ ለሚሰሩ በርካታ የልማት ስራዎች በኔነት ስሜት በጋራ መከወን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments