ዲጅታል ኢትዮጵያን እዉን ማድረግ በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጳጉሜ 5 የነገዉ ቀን የ19 ፕሮጀክቶች ሲስተምና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ምርቃት ስነ-ስርዓት ተካሄደ
ITDB፦ ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም
በመርሃ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ ፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲውት ምክትል ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ታዬ ግርማ ፣ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እንዲሁም የተቋማት ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን የመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ ጳጉሜ 5 የነገዉ ቀን ዲጅታል ኢትዮጵያን እዉን ማድረግ በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ መሆኑን ገልፀዉ የከተማ አስተዳደሩ በ2030 ከግብ ለማድረስ ካስቀመጣቸዉ ስድስት የስማርት ሲቲ አምዶች ስማርት ገቨርናንስ አንዱ መሆኑን አመላክተዋል። በመሆኑም በዛሬው ዕለት የ19 ፕሮጀክቶች ሲስተምና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ምርቃት ስነ-ስርዓት መሆኑን ገልፀዉ የለሙ ሲስተሞችን ወደ ስራ በማስገባት ቀጣይነቱን ማረጋገጥና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ እንደሚገባና ከዚህም ባሻገር በቀጣይ 75 አገልግሎቶችን ለማዘመን መታቀዱን ጠቁመዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች እዉን እንዲሆኑ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተያያዘም የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የሆኑት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላፈዉ ቢሮዉ ዘመኑ የሚጠይቀዉን የቴክኖሎጂ ልማት እንቅስቃሴዎች ሀገር በቀል በሆነ አቅም ሲስተሞችን አልምቶ በማስመረቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ይህንን የፈጠራ ስራ ዕዉን እንዲሆን የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አያይዘውም አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘትና የህብረተሰቡን ዕንግልት መቀነስ የሚያስችል የአዲስ መሶብ አገልግሎት ተግባራዊ የማድረግ ሂደት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰዉ የፈጠራ ስራዎች መዳበርና ዘላቂነት ያለዉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቢሮዉ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በቢሮው የከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ተቋማት አገልግሎቶቸዉን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ በሰራቸው በርካታ ስራዎች በተለይም በሶፍትዌር ልማት ስራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቢሮ ስራተኞች የዕዉቅናና ምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። በመጨረሻም የክብር እንግዶቹ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የለሙ ሲስተሞች በተቋሙ ሾው ሩም በመገኘት ምልከታ አካሂደዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments