LHRIS ሲስተም መሠረት ልማት ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ
ITDB፦ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም
በዉይይቱም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎች፣INSA ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር እና ባለድርሻ አካላት የተገኙበት ሲሆን የዉይይቱ ዋና አላማ LHRIS ሲስተምና መሰረተ ልማት ያለበትን ሁኔታ መገምገምና መካተት ያለባቸው ተግባራት በማመላከት አገልግሎቱን ለሚሰጡ አካላት ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር ማስገባት ላይ ያለመ ሲሆን በዚህ ሲስተም አማካኝነት ተገልጋዩ ባለበት ስፍራ ከአስርአንድ ተቋማና አራት መሬት ነክ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት ፈጣን ቀልጣፋ ፍትሀዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ መስጠት ማስቻል ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል።
በመሆኑም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ መካተት ያለባቸውን ቀሪ ተግባራት በማካተት በአጭር ግዜ ዉስጥ ወደ ተግባር መግባት እንደሚገባና በየግዜው ክትትልና ድጋፍ በማድረግ መሻሻያዎችን ማካሄድ እንዳለበት አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
                                
Leave Your Comments