የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ከሳዉዝ ኮርያ የመጡ ልኡካን ቡድኖች ጋር ዉይይት አካሄዱ

ITDB፦ ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ከሳዉዝ ኮርያ የመጡ ልኡካን ቡድኖች ጋር ዉይይት አካሄዱ። የዉይይት መርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ የተጀመረውን የስማርት ሲቲ ፅንሰ ሀሳብና የዲጅታል ቴክኖሎጂ ከከተማ መስተዳድሩ ጋር በመሆን ዳር ማድረስና የሳዉዝ ኮርያን መልካም ተሞክሮ ወደ አዲስ አበባ ማዉረድ ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

በዉይይቱም የቢሮ ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላትና ከሳዉዝ ኮርያ የመጡ ልኡካን ቡድኖች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ መዲናችን በርካታ ሀብት እንዳላትና አብሮነቱ ከተማዋን ስማርት ከማድረግ አንፃር የጎላ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀዉ በዚህ ዉይይት አብሮነትን የምናስቀጥልበትና በጋራ ለመስራት የተዘረጋ ትልቅ ድልድይ መሆኑን አመላክተዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የስማርት ሲቲ ፅንሰ ሀሳብ እና ስድስት አምዶች እንዲሁም ዲጅታል ሰርቪስን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከዚህም ባሻገር በተቋሙ ለምተዉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ሲስተሞች አመላክተዋል።

በቀረበዉ ገለፃ ላይ መሰረት ያደረገ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የቀረብ ሲሆን ለአብነት ያህል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራትና ወደ ፊት ምን እንደታቀደ፣ ተቋማትን ከማቀናጀትና ደህንነቱ የተጠበቀ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት አንፃር ምን እየተካሄደ እንደሆነ፣ የኔትዎርክ ኮኔክቲቪቲና ዳታ ክላዉድ በተመለከተ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ። በመሆኑም በተነሱ ጥያቄዎች ላይ የሚመለከታቸዉ ዘርፍ ሀላፊዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም የስማርት ሲቲ ስድስት አምዶች፣ ሮቦትና ሆሎግራም በመዘዋወር የመስክ ምልከታ በማካሄድ እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት በማድነቅና የአንድነት ስሜትን በመፍጠር መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments