በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ቀጣይ ሳምንት የሚካሄደዉ መርሃ-ግብር ላይ በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችል ዉይይት ተካሄደ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ቀጣይ ሳምንት የሚካሄደዉ መርሃ-ግብር ላይ በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችል ዉይይት ተካሄደ

********************

ITDB፦ ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም

የዉይይት መርሃ-ግብሩ ዓላማ የከተማ አስተዳሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገር ዜጎች ለሚገኙበት መርሃ ግብር የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለጎብኝዎች ከአጋር ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ግልዕ አጭር ሳቢ ገለፃን ማድረግ የሚቻልበት መንገድ መፍጠር ነዉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላፈዉ መርሃ ግብሩን ጥሩና ሳቢ ለማድረግ ሁላችንም በባለቤትነት መንፈስ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባና የፕሮጀክቶችን ሰነድ ሙሉ በሙሉ በማጠናጠቅ እስከ ሚቀጥለዉ ሳምንት ለእይታ ክፍት ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ከቢሮ ጋር የሚሰሩ አጋር ተቋማት ማከናወን ስላለባቸዉ ተግባራት ሰፌ ገለፃ አድርገዉ በመጨረሻም ከተሳታፌዎች ለተነሱላቸዉ ጥያቄ እንዲሁም ሀሳብ አስተያየቶች ምላሽ በመስጠት ለዝግጅት የሚሆነዉን የማሳያ ስፍራ አስጎብኝተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments