የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ ነሐሴ 5/2017ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ። በዚህ መርሃ ግብር ዕውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የወርቃማ ሰኞ ዋና ዓላማ ሳምንቱን በጥሩ መንፈስ ለመጀመር ያለንን ልምድና ተሞክሮ ለሌሎች የምናካፍልበትና ግንዛቤን በመፍጠር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የምናስቀምጥበት መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ “ubuntu” በሚል ርዕስ የቢሮው ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ግሩም አብተው የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል። በዕውቀት ሽግግሩም Ubuntu ማለት I am because of we are የምል ጥልቅ ሀሳብን በውስጡ የያዘ አፍሪካዊ ፍልስፍና መሆኑንና ትርጉሙም "እኔ ማለት በእኛ ውስጥ ነኝ" የሚል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስርን የሚያጠናክር እንደ እኛ አይነት ብዝሃ ማንነት ላላቸው ሀገራት እድገትና ሠላም መሰረታዊ የሆነ ሀሳብ መሆኑ አንስተዋል።

በተያያዘም ደቡብ አፍሪካ በኔሊሴን ማንዴላ ዘመን የአፓርታይድ ስርአትን አፍርሳ አሁን ያለውን የፖለቲካ ስርአት ስትገነባ ከመበቃቀል ይልቅ የይቅርታንና የትብብር አቅም ጎልቶ አሸናፊ እንዲሆንና የበቀልና የቂም እሳቤ ቦታ እንዳያገኝ ትልቅ ሚና የተጫወተው እሳቤ የኡቡንቱ (Ubuntu) እሳቤ መሆኑን አንስተው እኛም እንደ ሀገርም እንደ ተቋምም ይህን የእኛን የአፍሪካዊያንን እሳቤ ተግባራዊ በማድረግ በብዝሃነታችን ውስጥ ያለውን እድል አጉልተን ፈተናውን ለመሻገርና ወደ የምንፈልገው ዘላቂ ሠላምና ልማት መድረስ እንደምንች አመላክተዋል። ብዝሃነት ተፈጥሯዊ በመሆኑ ተፈጥሮ እድልና መልካም ሶጦታ እንደ መሆኑ መጠን ሰው ሰራሽ የሆኑ ደካማና ጎታች አስተሳሰቦችን ሙሉ በሙሉ ለመሻገር አሁን በብልጽግና በጀመርነው የመሃል ፖለቲካ መንገድና የወል ትርክታችንን በማጠናከር በኡቡንቱ እሳቤ ዘላቂ ማድረግ ይገባናል በማለት ሀሳባቸዉን ገልዋል።

በመጨረሻም በቢሮ ሀላፊ አማካኝነት ባለፈዉ ሳምንት የተከናወኑና በቀጣይ ትኩረት በሚፈልጉ ስራዎች ላይ አቅጣጫን በማመላከት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments