
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት ኤጀንሲ መሰረተ ልማት ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙርያ ዉይይት አካሄደ
ITDB፦ ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም
በዉይይቱም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎች፣ የቢሮ ዳታ ሴንተር ክላዉድ ማኔጅመንት ዳይሬክተር፣ የኤጀንሲዉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የዉይይት መርሃ-ግብር ዋና ዓላማ በኤጀንሲ መሰረተ ልማት ላይ ያጋጠሙ ላይ የወያየትና የመፍትሔ ሀሳቦችን ማስቀመጥ ነዉ።
የቢሮ ዳታ ማዕከል ክላዉድ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ የኔጌጥ በለጠ የሲቪል ምዝገባ ነዋሪነት ኤጀንሲ መሰረተ ልማት ዙርያ የተከናወኑ ስራዎች አጭር ሪፖርት ያቀረብ ሲሆን በሪፖርቱም የተከናወኑ ተግባራት፣ በዳታ ሴንተሩ ያጋጠሙ ችግሮች፣ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ዳሰዋል።
በመጨረሻም በቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየቶች የቀረብ ሲሆን በሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎችና ሀላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
መረጃዎችንተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments