
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎች ጋር ዉይይት ተካሄደ
ITDB፦ ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም
የዉይይት መርሃ-ግብር ዋና ዓላማ የ2018 በጀት ዓመት ፌዚካል ስራዎች የዝግጅት ስራ ለመጀመር ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ የተናበበ ዕቅድ ማዉረድና ቁልፍና አበይት ስራዎችን በአግባብ ለማስፈጸም በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የከተማዋን ስማርት ሲቲ ዕቅድ እና የቢሮ ስትራቴጂክ ዕቅድ ለማሳካት የተያያዙ ግቦች ዓላማዎችና ተግባራት በመፈፀም በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲፈጠር የሚያስችል ዉይይት ተካሄደ።
በዉይይቱም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎች፣ የክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ፌዚካል ስራዎች ዕቅድ ቀርቧል።
በቀረበዉ ዕቅድ ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከመዋቅርና ሰራተኛ ምደባ፣ በቂ የግንኙነት ግዜን አለመኖርን፣ በቂ ድጋፍና ክትትልን አለማግኘት፣ የባለሙያዎ ጥቅማጥቅም በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸዉ አካላትና ም/ቢሮ ሀላፊዎች ጥያቄዎችን እንደግብአት በመዉሰድ ምላሽ ሰጥተዉበታል።
በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ካስቀመጡ በኅላ የግንኙነት ግዜ በወር አንዴ እንደሚካሄድና የሚጋጥሙ ፈተናዎችን ተሻግረን በጥሩ መንፈስ ስራዎችን መከወን እንደሚገባ በማመላከት እስካሁን ለተከናወኑ ተግባራት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments