
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የግዥ አፈጻጸም ኦዲት የመውጫ ውይይት ተደረገ
ITDB፦ ነሐሴ/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከ2008 ጀምሮ እስከ 2017 በጀት ዓመት የተፈጸሙ የቴክኖሎጂ ግዥ ሂደት ኦዲት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ቢሮ ባለሙያዎች የተደረገ ሲሆን በተደረገው የኦዲት ውጤት ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጉዳዩ በቀጥታ የምመለከታቸው የስራ ክፍሎች በተገኙበት የመውጫ ውይይት ተደርጓል።
በተደረገው የመውጫ ውይይት በጥንካሬና በድክመት የተለዩ ጉዳዮች ቀርበው የጋራ መግባባት በመፍጠር በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውንም ጉዳዮችን በመለየት ትምህርት በሚሰጥ መልኩ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሐመድ ለቀጣይ ስራዎች ትምህርት በሚሰጥና አጋዥ በሚሆን መልኩ የተደረገ የኦድት ስራ መሆኑን በማንሳት የፋይናንስ ቢሮንና አመራሮችን እንዲሁም የኦዲት ባለሙያዎችን በማመስገን በቀጣይም በፋይናንስ ቢሮ በኩል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሚፈልጋቸውን ድጋፎች በማንሳት የእለቱን መድረክ ቋጭቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments