የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ E-SCHOOL ሲስተም ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ

ITDB፦ ነሐሴ/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለት/ቢሮ ያስለማዉ E-SCHOOL ሲስተም በከተማ መስተዳደሩ ስር ያሉ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ኦንላይን ከመመዝገብ ጀምሮ የትምህርት ተቋማትን አጠቃላይ መረጃዎች ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ ማከናወን የሚያስችልና ከዚህም ባሻገር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን የሚያከናዉን ሲስተም መሆኑ ይታወሳል በመሆኑም ሲስተሙ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ማጥበብ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ። በዉይይቱም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በዉይይቱም ሲስተሙ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ማለትም በ2017 አካዳሚክ ካሌንደር መጠናቀቅ የሚገባቸው መረጃን የማደራጀት ተግባራት በተገቢዉ ጊዜ ለማጠናቀቅ፣ የ2018 አካዳሚክ ካሌንደር ምዝገባ ማስጀመርና በሂደት በከተማ መስተዳድሩ ስር ያሉ ያሉ የግል ት/ቤቶች ሲስተም ዉስጥ ማስገባት የሚቻልበት መንገድ መፍጠር የሚያስችል ሰፊ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ መካሄድ ስላለባቸዉ ተግባራት የመፍትሔ ሀሳብና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments