በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጠቅላላ ካዉንስል አባላት ዉይይት አካሄዱ

ITDB፦ ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም

በዉይይቱ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ መሰረተ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የየዘርፉ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የተገኙ ሲሆን የዉይይት መርሃ-ግብሩ ዓላማ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ካስኬድ ማድረግና በቀጣይ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ መከናወን ስላለባቸው ተግባራት፣ የቀድሞ ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት አደረጃጀት በተመለከ ቀጣይ የሚኖረዉ መስተጋብር ምን መምሰል እንዳለበት ዉይይት ማካሄድና በቢሮው ሀላፊ አማካኝነት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ማስቀመጥ ነዉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የቢሮ ዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ የ2018 በጀት ዓመት ፌዚካል ስራዎች ዕቅድ ግብ ተኮር ተግባራት የቀረበ ሲሆን በየዘርፉ የሚመለከታቸውን ስራ በመማላከት ከማቀድ ባለፈ እስከ ባለሙያ ድረስ ወርዶ ማወያየት እንደሚገባ አመላክተዋል። በመቀጠልም በተቀመጡ አጀንዳዎች ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየት ተነስቷል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ቀጣይ የትኩረት አቅጣዎችን ያስቀመጡ ሲሆን ይህም የዕቅድ ክፍሉ ባለበት ሁሉም ዳይሬክተር ዕቅድ ማከፍፈል እንደሚገባ እና በቀጣይ ግምነማ እንደሚካሄድ፣ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ የተቀመጡ የመፍትሄ ሀሳቦችን ተግባር ላይ ማዋል እንደሚገባ፣ የክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አስተባባሪዎችን በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት ማወያየት መሆኑን አመላክተዉ የዝግጅት ምዕራፉን እንከን አልባ በሆነ መልኩ ስራዎችን ማከናወን ከተቻለ የትግበራዉ ምዕራፍ ዉጤታማ እንደሚሆንና በትኩረት ልንሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments