
የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር
ITDB፦ ሐምሌ 28/2017ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የወርቃማ ሰኞ መርሃግብር ዋና ዓላማ መነቃቃትና የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የአንዱን ዘርፍ ስራ ሌላዉ አዉቆ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት ማካሄድ ላይ መሆኑን ገልፀዉ "johari window" በሚል ርዕስ የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል።
በዕውቀት ሽግግሩም
- founder
- influence of model
- use of johari window
በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሳሌ በማስደገፍ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላቹ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments