
ከኦሮሚያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ፐብሊክ ሰርቪስ የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የመሶብ እንቅስቃሴን ላይ ትኩረት ያደረገ የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ
ITDB፦ ሐምሌ 25/2017ዓ/ም
ከኦሮሚያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ፐብሊክ ሰርቪስ የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እየተሰራ ያለውን የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ያደረገ የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ፡፡
የልምድ ልዉዉጡ ያተኮረው በቢሮው እየተሰራ ያለውን አዲስ መሶብ ፕሮጀክት ተቋማትን የማቀናጀት ስራ እየተከወነ ያለበት መንገድ የልምድ ልዉዉጥ ማካሄድ ሲሆን በዚሁ መርሃ ግብር የቢሮው ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ም/ቢሮ ሀላፊዎች እንዲሁም ቴክኒካል ኮሚቴ ተገኝተዋል፡፡
የቢሮው የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ የኮሚቴዎቹን አወቃቀር፣ በመጀመሪያ ዙር ወደ አገልግሎቱ የሚገቡት የመጀመሪያዎቹ 13ቱ ተቋማት በ107 አገልግሎቶችም መሆናቸውን ገልፀዉ ስራዎቹንም በትኩረት ለመስራት የተኬደበትን መንገድና የማቀናጀት ስራውም እየተሰራ እንደሆነ እንዲሁም አሁናዊ ሁኔታውን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ በበኩላቸው የመሶብ አገልግሎትን ተቋማትን የማቀናጀት ስራ እየተሰራበት ያለበት መንገድ ጥሩ እንደሆነ፣ ስራው ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው መሆኑ እና ለዚሁም የተመደቡት ሰራተኞች በከፍተኛ ዲሲፕሊን ስራዉን እየከወኑ እንደሆኑ ገልፀዋል።
በተያያዘም የአዲስ መሶብ ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት ከኢንተግሬሽን ጋር በተያያዘ በምሳሌ በማስደገፍ ሰፊና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም ከኦሮሚያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ፐብሊክ ሰርቪስ የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተደረገላቸው አቀባበል እና ገለፃ ደስተኛ መሆናቸዉንና በቀጣይ ባለሙያዎችን ይዘዉ በመምጣት ሰፊ ገለፃና የተግባር ምልከታ እንደሚያካሂዱ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments