
AutomaticInforcement and management system የፕሮጀክት አፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ
ITDB፦ ሐምሌ/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጃ ልማት ቢሮ ለትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እያስለማ ያለዉ AutomaticInforcement and management system የፕሮጀክት አፈጻጸም ለቢሮ አመራርና ባለድርሻ አካላት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የፕሮጀክቱ ዓላማ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተገልጋይ እንግልት እና ቅሬታን ለመቅረፍ እንዲሁም ወረቀት አልባ አገልግሎትን በመተግበር ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ ነዉ።
በመሆኑም የፕሮጀክቱ ፊዚካል ፕሮግረስ 90 ፐርሰንት ሲሆን የፕጀክቱ ፋይናንሺያል ፕሮግረስ 78.5 ፐርሰንት ላይ ደርሷል። በሪፖርቱም የሶፍት ዌር ማልማት እና አተገባበር፣ የሞባይል አፕ ልማትና አተገባበር፣ የሰርቨር ኢንሳቴሌሽንነና ኮንፍግሬሽን፣ የመረጃ ቋት የማቀናጀትና ዳታ ኢንኮዲንግ፣ የሲስተም ኢንተግሬሽን ስራና የብቃት ማረጋገጫን በተመለከተ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ሲስተሙ በትራፊክ ቁጥጥር እና በፓርኪንግ አገልግሎት የተሰማሩ ባለሙያዎችን የዕለት ተዕለት የስራ እንቅቃሴን ለመከታተልና ስህተቶች ቢኖሩ በቀላሉ ስህተት የፈጸመውን ባለሙያ መለየት፣ የተከፈለ ያልተከፈለ ክፍያዎችን በመጠንም በፐርሰትምማሳየት፣ የተያዙ ያልተያዙ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራዎችን ተጠቃሚው ሆነ ተቆጣጠሪው አካል በቀለሉ ማወቅ የሚያስችል ነዉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአውቶማተክ ኢንፎርስመንት ሲስተመን ወደ ስራ ለማስገባት ሁሉንም የባለስልጣኑን የቁጥጥር ባለሙያዎች ስልጠና እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የፓርኪንግ ሲስተምን ለማስጀመር የየቅርንጫፍ የፓርኪንግ ዳይሬክቶሬት እና ቡድን መሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና እንዲያገኘ በማደረግ ማህበራትን አሰልጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል።
በመጨረሻም ቀሪ ተግባራትን በመከወንና የኢንተግሬሽን ሥራው በተመለከተ ከኢትዮጵያንግድ ባንክ በሁሉም የዲጂታል አማራጮችን ከመጠቀም ባሻነር ከቴሌ ብር ጋር በማቀናጀት በአጭር ግዜ ዉስጥ ለመረካብ ስምምነት ላይ በመድረስ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments