በአዲስ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ላይ ው...

image description
- In Training    0

በአዲስ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ላይ ውይይት ተካሄደ

በአዲስ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ላይ ውይይት ተካሄደ

************

ITDB፦ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም

በአዲስ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት አሁናዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ። በውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች እና የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተገኝተዋል።

በውይይት ላይ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዮናስ ደምሰዉ ሰፊ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በገለፃቸው የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ከፌደራል ጀምሮ አስካሁን ድረስ የተሰሩትን ስራዎች ማካተቱንና ቡድን መደራጀቱን፣ በ13 ተቋማት ያሉ 107 አገልግሎቶች መመረጣቸውነ አገልግሎቶቹ ከሲስተም ጋር መሰራታቸውን፣ የማቀናጀት ስራ እየተሰራ መሆኑ፣ ሲስተም ላለማላቸዉ የማልማት ስራ መሰራቱን፣ የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ተቋማት ችግሮቻቸው መፈታታቸውን ገልፀዋል። ከዚህም አንፃር ስምንት ተቋማት በጥሩ የአፈፃፀም ሁኔታ ላይ፣ ሶስት በመካከለኛ እና ሁለቱ ድጋፍ እና ክትትል የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ከዚህም ባሻገር በአዲስ መሶብ የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎች መሰራታቸውንና ባጠቃላይ መሶብ ከመጀመሪያው ጀምሮ እስካሁን ድረስ የሄደበትን አግባብ በዝርዝር አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የኮሚቴዎች አወቃቀርና የፌዴራል ተቋማት እያደረጉት ያለው ድጋፍ ትልቅ መሆኑን እንዲሁም የመሶብ ፅንሰ ሃሳብ ከዚህ በፊት የነበሩትን ሲስተም እና መሰረተ ልማት ላይ ያሉትን ችግሮችን የሚያቃልል መሆኑን፣ በአዲስ መሶብ ፕሮጀክት ላይ ለሶስት ሳምንት ሙሉ በሙሉ ከስራው ሳይለዩ የሰሩ የIT ዳይሬክተሮች በስራ ላይ በትጋትና ጠንካራ የስራ ባህል እንደነበር ገልፀዉ የፌዴራል ተቋማትንም እገዛ አድንቀዋል።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ መዲናችን ትልቅ የለዉጥ ጎዳና ላይ መሆኗንና እነዚህ መሻሻሎች የሚጠበቁ መሆናቸዉን ገልፀዉ ለዚህም የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረዉ አመላክተዋል። በተያያዘም የነበሩትን ክፍተቶች ላይ እርምት በመወሰዳቸውን አድንቀዋል። የፌዴራል ተቋማት በነኚህ ስራዎች መካተት አስፈላጊ መሆኑንና ታሳቢ መደረግ እንደሚገባው ገልፀዉ አስፈላጊነቱ የጎላ በመሆኑ በርካታ ተቋማት አገልግሎቱን ፈልገው መምጣታችው የማይቀር በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶበት እንዲሰራ በማሳሰብ ለተሰሩት ስራዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ የመሶብ ተፈላጊነት በጣም እየሰፋ የሚሄድ መሆኑንና ስራዉ ሲያከናዉን የነበረ ቡድን አመስግነዉ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰራር ዘመኑን ያልዋጀ እንደነበርና ነገር ግን አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ ጥሩ እየሄደ እንደሆነ በመማመላከት በተጨማሪም ቀሪ ስራዎችን በጋራ መገምገም እነደሚገባ እና በብርቱ መንፈስ መስራተ አለብን ብለዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments