
የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር
የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር
*******************************
ITDB፦ ሐምሌ 21/2017ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ባለፈዉ ሳምንት የተቋማት ግምገማ መካሄዱንና ከ27 ተቋማት 80.6 በማምጣት 19 የወጣን መሆኑንና ይህንን ዉጤት ለማሻሻል እንዲሁም ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በርትተን መስራት እንደሚጠበቅብን ገልፀዋል።
የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን "Explanation of automatic evaluation metrics for natural language processing system " በሚል ርዕስ የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል።
በዕውቀት ሽግግሩም
- machine translation
- paragraph evaluation system
- chat bot
- paraphrase generation
በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን
በተያያዘም ያለንቀት ተቋም ትልቅና በርካታ ተግባራትን የሚፈጽም ነገ ብሩህ ተስፍ ያለዉ መሆኑን ገልፀዉ ስራችንን በቅንነትና ቀታማኝነት ጠንክረን ልንሰራ እንደሚገባ በማመላከት መልካም የስራ ሳምንት ተመኝተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments