
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች የማጠቃለያ ሪፖርት ተገመገመ
ITDB፦ ሐምሌ፦ 17/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት መልካም አስተዳደር የተፈቱ ችግሮች፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ማጠቃለያና በ2018 በጀት ዓመት መልካም አስተዳደር የሚፈቱ ችግሮች እንዲሁም ዕቅድ ዉይይት ተካሂዷል።
የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የዛሬዉ ፕሮግራም ዓላማ በ2017 በጀት ዓመት ከተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በመገምገም በ2018 በጀት ዓመት ዲጅታል መስተጋብራችን ምን መምሰል እንዳለበትና ግልፀኝነት፣ ቀልጣፋና ፍትሀዊነት የሰፈነበት ችግር ፈቺ ሲስተም ለመዘርጋት ጠንካራ ህብረት ፈጥረን በትስስር መስራት እንደሚገባ በማመልከት መርሃ ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ዓመት ከተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ያቀረቡት የለዉጥ ዳይሬክተር አቶ ግርማ ከበደ የሪፖርቱ ዓላማ በበጀት ዓመቱ በእቅድ ትግበራ ሂደት ቢሮዉ ብቻውን ማሳካት በማይችላቸው ተግባራት ላይ ሴክተር ተቋማትን በመለየትና ስምምነት በመፍጠር ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤታማነት ለማሳካት መሆኑን ገልፀዉ የትስስሩ አስፈላጊነት፣ የትስስሩ መርሆዎች፣ የሪፖርቱ ወሰን፣ የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች፣ የቢሮ ባለድርሻ አካላት ዝርዝር፣ የመልካም አስተዳደር መርህ ምላሽ ሰጪነት ለማረጋገጥ፣ በ2017 በጀት ዓመት የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች በዝርዝር ዳሰዋል።
በቀረበዉ ዕቅድና ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረጉ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ እና የቢሮው ጽ/ቤት ሀላፊ ምላሽ ሰጥተዉበታል። በመጨረሻም ከተቋማት ጋር የ2018 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ አሰራር ስምምነት ዕቅድ ሰነድ በመፈራረም የዕዉቅናና ሽልማት መርሃ ግብር ተከናውኗል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments