
የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር
ITDB፦ ሐምሌ 14/2017ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆኑ የቢሮ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስታንዳርድ ሬጉላቶሪ ቡድን መሪ አቶ ዮናስ ደምሰዉ "Sharing knowledge in IT breaking silos bulging" በሚል ርዕስ የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል።
በዕውቀት ሽግግሩም
- Why knowledge sharing is critical in IT
- IT specific barriers
- interactive poll
- How IT team share knowledge effectively
- Building a knowledge sharing culture in IT
- IT specific engagement idea
በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን
በተያያዘም የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ወርቃማ ሰኞ ለስራ ዉጤታማነት ጠቃሚ የሆኑ አጀንዳዎች እንደሚነሱና ተገቢዉ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ገልፀዉ ባለፈዉ ሳምንት የተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ያስቀመጡ ሲሆን በዚህ ወር የምናስመርቃቸዉ በርካታ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩ በማመላከት መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላቹ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments