integrated food and health car...

image description
- In Training    0

integrated food and health care regulatory system ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ

ITDB፦ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መድሀኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ያለማዉ integrated food and health care regulatory system ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ።

የስልጠናዉ ዋና ዓላማ integrated food and health care regulatory system ማለትም ከወረቀት ነፃ የሆነ ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ሙሉ ለሙሉ ከማዕከል እስከ ክላስተር ለመተግበር በሚያስችል መልኩ የተቋሙን ሰራተኛ ማብቃት ላይ ያለመ ነዉ።

ስልጠናው በርካታ ሞጁሎች ያሉት ሲሆን ከነዚህም መካከል የጤና ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የጤና ባለሙያዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የጤና ተቋማት ቁጥጥር፣ የምርትና ጥራት ደህንነት ፍተሻ ላብራቶሪ፣ ሜድኮሌጋለና የተቋሙ ቢዝነስ ፕሮሰስ በዝርዝር የሚዳስስ ይሆናል። ስልጠናው በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አማካኝነት በሁለት ዙር ለ300 የተቋሙ ሰራተኞች የሚሰጥ መሆኑን የስልጠናው አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments