
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 7ተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሄደ
ITDB፦ ሐምሌ 11/2017ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 7ተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቀለም መርቅ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ አካሄደ።
በመርሃ ግብሩ የቢሮ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የአራዳ ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ የተገኙ ሲሆን የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግሩም አብተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ ለ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሃ ግብር እንኳን አደረሳችሁ በማለት አረንጓዴ አሻራ ማኖር ማለት የሃገራችንንና ከባቢያዊ አየር መንከባከብ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ሠራተኛ በሀላፊነት የበኩሉን አስተዋፆኦ እንዲያበረክት አሳስበዋል።
የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ባስተላለፍት መልዕክት መዲናዋ ከሰኔ ወር ጀምሮ በዘጠና ቀናት ፕሮጀክት በርካታ ተግባራት እያከናወነች መሆናን ገልፀዉ ባለፈው አመት 30,000 ችግኞች እንደ ቢሮ ተክለን እንደነበርና ባለፈው ሳምንትም የመንከባከብ እና ተጨማሪ የ200 ችግኞች መተከሉን አመላክተዋል። አያይዘዉም ከመትከል ባሻገር መንከባከብ ትልቅ ድርሻ እንዳለዉ አስታወስ በዛሬዉ ዕለት ከ700 በላይ ችግኞችን የመትከል ተግባር እንደሚከናወንና በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለዉጥ ችግሮች ለመቆጣጠር በምንችለዉ ልክ የመዲናዋን የግሪን ሌጋሲ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል። በመጨረሻም ለችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መሳካት ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ላበረከቱት የአራዳ ክ/ከተማ አመራሮችንና ቀለመ ወርቅ ትምህርት ቤት በማመስገን ከመትከል ባሻገር በቅርበት የመንከባከብ ተግባር እንደሚከናወን በማመላከት የችግኝ ተከላውን መርሃ ግብር በይፋ አስጀምረዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments