“የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ የክፍለ ከተ...

image description
- In Technology Trends    0

“የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ የክፍለ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አመራሮችና ባለሞያዎች ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት መጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባቸዋል" ፦አቶ አዋሌ መሐመድ

ITDB ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ በበይነ መረብ (on-line) አየተሰጠ የነበረውየ12 ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት ፈተናው ከመጀመሩ አስቀድሞ እስኪጠናቀቅ ድረስ በተለያየ መንገድ ሲተጉ የነበሩትን ባለሙያና አመራሮች የላቀ ክብርና ምስጋና እንደሚገባው ይገባቸዉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ 109 የመፈተኛ ጣቢያዎች 50,800 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ (on-lime) ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፣ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በማዕከል እና በክፍለ ከተሞች የሚገኙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች በመተባበር በሁሉ የፈተና ጣቢያዎች የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ዝርጋታና የኮነክቲቪቲ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ ሂደቱም መድናችን አዲስ አበባ ስማርት ሲቲ ጉዞ የሚያፋጥንና የስማርት ፒፕልን እዉን ለማድረግ የሚረዳ መሆኑንም የቢሮ የክላውድና ዳታ ሴንተር ዳይሬክተር አቶ የኔጌጥ በለጠ ገልፀዋል፡፡

በዚህ የ12ኛ ክፍል ፈተና የአብርሆት ቤተ መፅሐፍትና የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የፈተና ጣቢያዎች የመፈተኛ መሳሪያዎችን ከማቅረብ አንስቶ እስከ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በፈተናው ሂደት ላይ ሙያዊ እገዛ በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በርካታ ባለሙያዎችን መድቦ የሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments