የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ፌዚካል ስራዎች ዕቅድ ተገመገመ

ITDB፦ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም

የዕቅዱ ዓላማ የከተማዋን ስማርት ሲቲ ዕቅድ እና የቢሮ ስትራቴጂክ ዕቅድን ለማሳካት የተያዙ ግቦች፣ ዓላማዎችና ተግባራት በመፈፀም በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲፈጠር ማስቻል ነዉ።

በዕቅድ ግምገማዉ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የዛሬዉ መድረክ ዓላማ የ2018 በጀት ዓመት ፌዚካል ስራዎች መገምገምና የዝግጅት ስራን በመጀመር ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የተናበበ ዕቅድ ማዉረድ መሆኑን ገልፀዉ ከዚህም ባሻገር ቁልፍና አበይት ስራዎችን በአግባብ ለማስፈፀም በቂ ግንዛቤን መፍጠርና የተጠያቂነት ስሜት ማጎልበት እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ ስርዓታችን ምን መምሰል እንዳለበት የሚያመላክት መሆኑን ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ፌዚካል ስራዎች ዕቅድ ያቀረቡት የቢሮ ዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ ሲሆኑ መነሻ ሁኔታዎች፣ የ2018 ቁልፍ ስራዎች ዕቅድ፣ የ2018 ዓበይት ስራዎች ዕቅድ፣ የማስፈፀምያ ስልትቶች (አቅጣጫዎች) በዝርዝር ዳሰዋል።

በተያያዘም በቀረበዉ ዕቅድ ላይ መሰረት ያደረ ሀሳብ አስተያየት ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የዕቅድና በጀት ዳሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ እንደግብአት በመዉሰድ ምላሽ ሰጥተዉበታል። በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ላይ ተጨማሪ ሀሳብ በመስጠት በዕቅድ ዉስጥ መካተት ስላለባቸዉና መታረም ስላለባቸው ጉዳዮችን፣ መከናወን ስላለባቸው ተግባራት አቅጣጫ በመስጠት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments