የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር

ITDB፦ ሐምሌ 7/2017ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆኑ ኦፕሬሽንና አገልግሎት ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ፈለቀ ባለፈዉ በጀት ዓመት የታቀዱ ተግባራት በተገቢዉ መንገድ ማከናወናቸውንና ለስራ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር ቀሪ የቢሮ ዕድሳት ስራዎች መካሄዳቸውን ገልፀዉ በዛሬዉ መርሃ ግብር "Became who we are" በሚል ርዕስ የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል። በተያያዘም ባለፈዉ ሳምንት የተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ያስቀመጡ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የያዝናቸዉን ስራዎች አጠናቀን ለ2018 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ስራን የምናካሂድበትና በዝግጅት ምዕራፍ በርካታ ተግባራትን ካከናወንን በትግበራ ወቅት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርልን በማመላከት መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላቹ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments