
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች የችግኝ የመንከባከብ ተግባር አከናወኑ
ITDB ፦ ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም
የአንድ ዛፍ ዋጋ የማይለካ ሲሆን ለአካባቢ ጥበቃ ዋስትና፣ የኃይል ምንጭ፣ የኢኮኖሚ ዋልታ እና የሰው ልጆች ጤና ጠበቃ ነው፡፡ ችግኝ ስንተክል በመሬት ላይ ብቻ ሳይሆን በሕይወታችን ውስጥ ኢንቨስት እናደርጋለን። ዛፍ በእያንዳንዱ ቅጠል፣ በእያንዳንዱ ሥር እና በእያንዳንዱ ቅርንጫፍ ላይ ጤናማ፣ አረንጓዴ እና የበለጠ ፋይዳ ያለው ተስፋን ይሸከማል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ከመትከል በላይ መንከባከብ ላይ ትኩረት በማድረግ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታዎችን እያበረከተ ሲሆን ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመሬት መራቆት የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመቀነስ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በምታደርገው ርብርብ ባለፉት ስድስት ዓመታት እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላና እንክብካቤ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እያስገኘ ነው፡፡
በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች "መትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ የችግኝ መንከባከብ እና መትከል ተግባር አከናወኑ።
የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የዛሬዉ መርሐ-ግብር የተካሄደበት ዋና ዓላማ በ2016 በጀት ዓመት የተተከሉ 30ሺህ ችግኞችን መንከባከብ፣ 200 ችግኞችን መትከልና ቀጣይ የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ማስጀመር መሆኑን ገልፀው ባለንበት የለዉጥ ሂደት እየተከናወኑ ካሉ በርካታ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነዉን ግሪን ሌጋሲ ከመትከል እስከ መንከባከብ ድረስ በመስራት ቢሮ የተግባር ማሳያ መሆኑን በማመላከት ለዚህም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተዉን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በቢሮው ስም አመስግነዋል። በተያያዘም በሚቀጥሉት ሳምንት በአራዳ ክ/ከተማ እያንዳንዱ ሰራተኛ አምስት ጉርጓድ በመቆፈር አምስት ችግኝ መትከል እንዳለበት በማመላከት ሁላችንም በጋራ በመሆን የሀገራችንን የአየር ንብረት ከኦዞን ሌየር መሳሳት እንታደግ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments