የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የክረምት የ90...

image description
- In Training    0

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የክረምት የ90 ቀን እቅድ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ተገመገመ

AITDB፦ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች የክረምት የ90 ቀናት የቢሮው እቅድ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ላይ ውይይት አካሄዱ።

የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሐመድ የዛሬ መድረክ ባለፈው ሰኔ መጀመሪያ የጋራ አድርገንና ስምሪት ወስደን ወደ ስራ የገባንበት የክረምት የ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን አንስተው ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን በመመኘት መድረኩን ከፍተዋል።

የ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴም እንዳሉት በ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ውስጥ የተያዙት ተግባራት በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን በማንሳት ለምሳሌ ለአቅመ ደካማ 12 አባወራ/እማወራ ወገኖች በቅርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እየተገነባ ያለው ጂ+2 መኖሪያ ቤት አፈጻጸም ወደ 80% መድረሱን፣ በዚህ 90 ቀናት ውስጥ ለማስመረቅ የተያዙ ፕሮጀክቶች አፈጻጸምና ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየሔደ መሆኑን፣ የመሶብ አገልግሎት ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን፣ የችግኝ ኩትኳቶ ስራ በእቅዱ መሰረት መከናወኑን፣ የማጠቃለያ ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተፈጸሙ መሆኑን፣ የሠራተኞች የናሽናል አይዲ ምዝገባ 86% መድረሱን፣ የኢትዮኮዴርስ ስልጠናና ሌሎችም ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ እንዳሉ አንስተዋል።

አጠቃላይ በቀረበው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ከሠራተኛው ሃሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ከዘርፍ አመራሮችና ከጽ/ቤት ኃላፊ ምላሽና ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ የማጠቃለያ ሃሳብና የቀጣይ አቅጣጫ በክቡር የቢሮ ኃላፊ ተሰጥቶ መድረኩ ተቋጭቷል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments