
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሠራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ዉይይት አካሄዱ
ITDB፦ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የቢሮው ማጠቃለያ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።
የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሐመድ የዛሬ መድረክ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ አቅደን ስንተገብር የቆየነውን የስራ ፍሬያችንን ብቻ ሳይሆን ሳናሳካ የቀረንባቸው ተግባራቶችንም በአግባቡ ፈትሸን በመገምገም ለውጤቱም ለክፍተቱም እያንዳንዳችን የነበረንን ድርሻ በተገቢው ወስደን በ2018 በጀት ዓመት የማስተካከያ እርምጃዎችንም በመውሰድ ወደ ተግባር ለመግባት የመንደርደሪያ መድረክ መሆኑን አንስተውል።
የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴም በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት በእቅዱ መሰረትና ከእቅድ በላይ መሳካታቸውን አንስተው ነገር ግን ደግሞ ከመረጃ አያያዝና የምጠየቁ መረጃዎችን በጊዜና በጥራት ለእቅድና በጀት ክፍል ከማድረስ አኳያ ጥቂት በማይባሉ የስራ ክፍሎች በኩል ከፍተኛ ክፍተት የነበረ መሆኑን ጠቁመው በ2018 በጀት ዓመት መደገም የለሌበት መሆኑን በአፅንኦት ገልፀዋል።
በቀረበው እቅድ ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረገ ከሠራተኛው ሃሳብ አስተያየተትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጥያቀዎች ላይ ከዘርፍ አመራሮችና ከጽ/ቤት ኃላፊ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የማጠቃለያ ሃሳብና የቀጣይ አቅጣጫ በቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments