
የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ
ITDB፦ ሰኔ 30/2017ዓ/ም
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በየሳምንቱ ሰኞ ማለዳ የሚደረገውን የወርቃማ ሰኞ መርሃ-ግብር ተከናወነ።
በመሪሃ ግብሩ ላይ የተቋሙን ሰራተኞች የሚያነቃቃ ሃሳብ የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሐመድ ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ርዕስ ላይ መሰረት ያደረገ ሰፋ ያለ ገለፃ ሰጥተዋል። በማነቃቂያ ንግግሩንም በህይወት እያለን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መድረስ ለሚገባን የማህበረሰብ ክፍል በመድረስ ለሌሎች የደስታ ምክንያት የመሆንን ያክል ሰውን የሚያረካ ነገር እንደሌለ አውስተው በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ስራ ላይም ከልብ በመሳተፍ የሚጠበቅብንን እንወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ ይሄንንም ቢሮ በጀመረው የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ እና ለአረንጓዴ አሻራ ማኖር እንቅስቃሴ ላይ ችግኞችን በመትከል ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ አካባቢያችንን የመጠበቅ ትልቅ ሀላፊነት አለብን በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል። ሠራተኞችም በመርሃ ግብሩ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የሚጠበቅ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው በማንሳት። አያይዘውም በወርቃማ ሰኞ መርሃ-ግብር ላይ አመራሩ ብቻ አስተማሪ የሆኑ ሃሳብ እንዲያቀርብ ከመተው ይልቅ ሁሉም ያለውን ለሌሎች ቢካፋል አስተማሪ እንደሚሆን በመጠቆም ይጠቅማል የምትሉትን ርዕሰ ጉዳይ ቀድሞ ለቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ግሩም አብተው በማሳወቅ በሚሰጠችሁ መርሃ ግብር መሰረት ማቅረብ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በመጨረሻም በሳምንቱ ውስጥ ታቅደው የተፈጸሙ አበይት ተግባራትንና በቀጣይ ሳምንት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት እቅድ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የቢሮ ሠራተኞች ምን እየተከናወነ እንዳለ መረጃ እንዲኖረውና በጋራ በመደጋገፍ የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል በማለት የቢሮ ኃላፊው አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments