ከተለያዩ ተቃማት የተውጣጡ የሱፐርቪዘዢን ቡድን...

image description
- In Training    0

ከተለያዩ ተቃማት የተውጣጡ የሱፐርቪዘዢን ቡድን አባላት የመሶብ እንቅስቃሴን ጎበኙ

ITDB፦ ሰኔ 27/2017ዓ/ም

ከአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ ኢንስቲቱት፣ ከፌደራል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ከፌደራል ሲቪል ስርቪስ ኮሚሽን የተውጣጡ የሱፐርቪዢን ቡድን አባላት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እየተሰራ ያለውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

ጉብኝቱ ያተኮረው በቢሮው እየተሰራ ያለውን በመሶብ ፕሮጀክት ተቋማትን የማቀናጀት ስራ ከምን እንደደረሰ መገምገም ሲሆን በዚሁ መርሃ ግብር የቢሮው አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የቢሮው የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ለሱፐርቪዥኑ ቡድን አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኅላ ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ የኮሚቴዎቹን አወቃቀር፣ በመጀመሪያ ዙር ወደ አገልግሎቱ የሚገቡት የመጀመሪያዎቹ 13ቱ ተቋማት በ107 አገልግሎቶችም መሆናቸውን ገልፀዉ ስራዎቹንም በትኩረት ለመስራት የተኬደበትን መንገድ፣ ችግሮች የመለየት ስራም መሰራቱንና የማቀናጀት ስራውም እየተሰራ እንደሆነ እንዲሁም አሁናዊ ሁኔታውም ጥሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ በበኩላቸው የመሶብ አገልግሎትን ተቋማትን የማቀናጀት ስራ እየተሰራበት ያለበት መንገድ ጥሩ እንደሆነ፣ ስራው ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው መሆኑ እና ለዚሁም ቢሮው ምቹ የስራ ቦታና ሎጀስቲክ እንዳዘጋጀ፣ ለስራውም የተመደቡት ታታሪ ሰራተኞች እንደሆኑ ገልፀው፣ እየተቀራረቡና እየተግባቡ መስራት ለዚህች ሃገር አስፈላጊ እንደሆነና ስራውንም ስንሰራ ጊዜ የለኝም በሚል መንፈስ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በተያያዘም ለጉብኝት የመጡትን የሱፐርቪዥን ቡድን አባላትን አመስግነው የሰጡትን አስተያየትም እንደግብአት በመዉሰድ ቢሮዉ እንደሚጠቀምበት ጠቁመዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments