
በኢትዮጵያ የህዋዌ ኢንተርፕራይዝ ድፓርትመንት ቡድን የስማርት ሲቲ መሰረት የሆነውን “one cloud, one network, one city’ የሚለውን ስትራቴጂ አስተዋወቁ
ITDB፦ ሰኔ 27/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ የህዋዌ ኢንተርፕራይዝ ድፓርትመንት ቡድን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስማርት ሲቲ መሰረት የሆነውን “one cloud, one network, one city’ የሚለውን ስትራቴጂ አስተዋወቁ። በዚህ የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው ኃላፊ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆኑ የኢንተርፕራይዝ ድፓርትመንቱ ዳይሬክተር Mr. Mengpei ስለ ስትራቴጂው ምንነት ገለፃ አድርገዋል። በተሰጠው ገለፃ ላይ መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኢንተርፕራይዙ ዲፓርትመንት ቡድን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ ስለነበራቸው ጊዜ እና ስለ ተሰጠው ገለፃ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዚሁም ወደፊት ቢሮዉ አብሮ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገልፀው የህዋዌ ቴክኖሎጂዎች ከዲጂታላይዜሽን አንፃር በፈጣን ሁኔታ ከጊዜው ጋር የሚጓዙ ከመሁኑ አንጻር ትኩረትን እየሳበ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል። አያይዘዉም በሃገራችንም በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን ያለበትን ሁኔታ አውስተው ይሄም ለዜጎቻችን በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ያለውን ፋይዳ አስረድተዋል። በዚህም ወደፊት አብረው ለመስራት ጥልቅ ፍላጎት የሚያሳድር መሆኑን ገልጠው ስለነበራቸውም ጊዜ በማመስገን መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments